ጤና ይስጥልኝ የነቅዐ ህይወት ጉባኤ ቤት ቤተሰቦች

ጉባኤ ቤቱ ቃለ ወንጌልን ከማስፋፋት አኳያ ከያዘው አላማ ጋር ተያይዞ በትምህርት ቤቱ ቅጽር ጊቢ ውስጥ የንዋየ ቅድሳት(መጻሕፍት) መሸጫ እየገነባ ይገኛል። ለእዚህም ሥራ ማጠናቀቂያ ባለ 32 ጌጅ 28 የጣርያ ቆርቆሮ አስፈልጎታል ።  የአንዱ ዋጋ 650 ብር ነው። ስለእዚህ የተባለውን ወጪ ሸፍነን ስራውን ለማስጀመር ብንተባበር!!!

 

በወለህ ነቅዐ ሕይወት የ4ቱ  ጉባኤ ቤት የሚሠራው አዲሱ የልማት ሱቅ እዚህ ደርሷል ልማት ክፍሉም የሱቁ ቤት ባያልቅም ሥራውን በቤቱ ሆኖ ጀምሯል በርታ በሉት
 ነገሩ እርፍ ይዞ ወደኋላ ማረስ የለም እንደተባለ ነው። በጥሩ ሁኔታ እንደሚቀጥል  ተስፋ እናደርጋለን።
ለአንድ ጉባኤ ቤት ሦስት ነገሮች ያስፈልጉታል ብለን በማመን ሦስት መርሖች አሉን እኒህም:-
1'እውቀት
2'ሕይወት
3'ልማት ናቸው
አንድ ሰው ለማወቅ ይማራል ባወቀው ይኖራል ለመኖርም ይሠራል ያለማል 
ይህም 
ሊሠራ የማይወድ አይብላ ያለው ነው ምሥጢሩም ሣይሠሩ መብላት በራሱ ሥርቆት ነው ነው።
"ጉባኤ ቤት የቤተ ክርስቲያን ማኅፀን ነው" 
"እናትን መደገፍ ለትውልድ ማሰብ ነው"
"ጉባኤ ቤትን መደገፍ በሊቃውንት ተፈጥሮ ላይ ተሳትፎ ማድረግ ነው"

Comments powered by CComment

ስብከቶች (Preaching)

  • 3383

    ሉቃስ ወንጌል ም። 18 ቁ። 1 __6

    1ሳይታክቱ ዘወትር  ሊጸልዩ  እንዲገባቸው የሚል ምሳሌ ነገራቸው፤ 2እንዲህ ሲል፤  “በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። 3በዚያችው ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፤ ወደ እርሱም እየመጣች፣ ‘ከባላጋራዬ ፍረድልኝ’ ትለው ነበር።  4 አያሌ ቀንም አልወደደም ፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፤ ‘ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ፣ ሰውንም ባላፍር፣ 5ይህች መበለት ስለምታደክመኝ፣ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ  እፈርድላታለሁ አለ።’  6ጌታም አለ፤ “ዓመፀኛው ዳኛ

    ...

    Read more: ዘወትር ጸሎት

  • 2634

    ቀሲስ ሕብረት የሺጥላ፣ በስብከታቸው ከዚህ በታች ያሉትን እና ሌሎች ጥያቄዎችን ያብራራሉ፤ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (link ) በመጫን ስብከቱን ያድምጡ።

    1. የመላእክት አፈጣጠር
    2. የመላእክት ቁጥር ሰንት ነው?
    3. መላእክት ሰራቸው ምንድን ነው ?
    4. ማማለድ ምን ማለት ነው 

    Read more: መላእክት

  • 2666

    (ኦሪት ዘፍጥረት ም.22  ቁ. 1.)

    ከነዚህ ነገሮች ቦኃላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው። እንዲህም አለው። አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፣ እንሆ አለሁ አለ። የምትወደውን አንድ ልጅህን ይሥሀቅን ይዘህ ወደሞርያም ምድር ኺድ እኔም በምነግርህ ባንድ ተራራ ላይ በዚያ ምሥዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ። አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፣ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሐቅን ከርሱ ጋር ወሰደ፣ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ ተነስቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ።  (ኦሪት ዘፍጥረት ም.22  ቁ. 1.)

    ከዚህ ኃይለቃል

    ...

    Read more: አብርሃም

  • 2654

    ማቴዎስወንጌል ም. 4 ቁ - 1

    ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስወንጌል ም. 4 ቁ - 1

    ከዚህ ኃይለቃል በመነሳት ቀሲስ ሕብረት

    ...

    Read more: ክርስቲያናዊ ጾም

  • 2155

    "እንሆ የእህትሽ የሰዶም ኀጢአት ይህ ነበረ። ትዕቢት ፣ እንጀራን መጥገብ ፣ መዝለልና ሥራ ምፍታት በርሷና በሴቶች ልጆቿ ነበረ ፣ የችግረኛውንና የድሃውንም እጅ አላጸናችም። " ሕዝቃኤል 16 ቁጥር 42

    ቀሲስሕብረትየሺጥላ፣ ከዚህ ኃይለቃል በመነሳት፣በስብከታቸውከዚህበታችያሉትንእናሌሎችጥያቄዎችን

    ...

    Read more: የሰዶም ኀጢአት

ማስታወቂያዎች

Login Form