ማቴዎስወንጌል ም. 4 ቁ - 1

ከዚህ ኃይለቃል በመነሳት ቀሲስ ሕብረት የሺጥላ፣ በስብከታቸው ከዚህ በታች ያሉትን እና ሌሎች ጥያቄዎችን ያብራራሉ፤ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (link ) በመጫን ስብከቱን ያድምጡ።

ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስወንጌል ም. 4 ቁ - 1

 

  1. አንድ ክርስቲያን ከተጠመቀ ቦሃላ የመጀመሪያ ስራው ምን መሆን አለበት ? ይህ ህጻናትን ይጨምራል?
  2. ጾም የነፍስ ምግቧ ፣ የስጋ ልጓም ትባላለች ? የጸሎት እናት ፣ የዝምታ እህት ትባላለች።
  3. መጸለይ የቸገረን ሰዎች በመጾም ጸሎትን ማግኘት መበርታት ይቻላል።
  4. ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ ምን ማለት ነው ?  ወደሚፈተኑበት ቦታ መሔድ አግባብ ነውን ?
  5. መንፈስ ወደ ምድረበዳ ወሰደው ስንል ምን ማለታችን ነው ? 

 

Comments powered by CComment