የእዚህ ድረገጽ አላማ ወንጌል ለሁሉ እንዲዳረስ አንድ ተጨማሪ  የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ድረገጽ (website) ማበርከት ነው ፣ በግልም ይሁን ከተለያየ ቦታ ጀማሪ ከሆኑ ክርስቲያኖች የሚቀርቡልንን መንፈሳዊ ጥያቄዎች ከመምህራን ጋር በመሆን በማጣቀሻ የተደገፈ መልስ እንዲያገኙ መርዳት ነው።

ፈቃድበዚህ ድረገጽ ላይ ያካፈልናቸው ድምጾችም ሆኑ መጣጥፎች ከድምጹ ባለቤቶችም ሆነ ድምጹን ከቀረጹት ባለሞያዎች የተገኘ ማረጋገጫ ባይኖርም ጥቂቶቹን መምህራን በስልክ በማግኘት ፈቃደኝነታችውን ገልጽውልናል። ለአብዛኛዎቹ መጣጥፎችና የድምጽ ቅጅዎች አሁንም ቢሆን የፈቃደኝነት  ማረጋገጫ ባናገኝም ከ ድረገጹ አላማና ጥቅም አንጻር እነደተለጠፉ እንዲቆዩ አድርገናል። ወደፊት በዚህ ገጽ ለማጋራት ላሰብናቸው መጣጥፎችም እንዲሁ።  ምንም አይነት ንግድና ከትርፍ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በዚህ ገጽ ላይ የማካፈል እቅድ ስለሌለን አላማው ከጅምሩ ግልጽ እንዲሆን እንፈለጋለን። ስለዚህ ድረገጽ አጀማመር ለማወቅ ይህን ይጫኑ። 

ያጋራናቸው ስብከቶችና መጣጥፎች በተፈለገ ጊዜ በቀላሉ ይገኝ ዘንድ በመልክ መልኩ አስቀምጠናል። የረቀቁ ፍለጋዎችን ( advanced search ) መጠቀምም ይቻላል። ተመዝግበን የተለያዩ ስብከቶችን እና መጣትፎችን ማጋራት፤ ጥያቄዎችን መጠየቅና ልምድ ማካፈል ያስችለናል። በተለይም በገነት ጽጌ ሰንበት ትምህርት ቤት ያለፋችሁ እግዚአብሔር ጸጋውን ያበዛላቹ ወንድሞችና እህቶች የምትጽፏቸውን መጣጥፎች በዚህ ድረገጽ በማጋራት ተደራሽነታቸውን በማሳደግና ያለስጋት ለብዙ ዘመን እንዲቀመጥ በማድረግ ለብዙዎች ህይወት እንዲሆኑ ማድረግ ትችላላችሁ።  ድረገጻችን በመረጃ ቋት የተደገፈ ማህደር ( database driven dynamic website) በመሆኑ በየጊዜው የሚጠበቅ ደጀን ማህደር ( regular cloud based archive and backup)ያለው ስለሆነ ከተለመደው ማህበራዊ ገጾች የተለየ ጥቅም አለው።  እንዳስፈላጊነቱ፣ ለአባላት ብቻ የሚጋሩ ( only registered members)  የተለያዩ ክፍሎችን በመጨመር ልንጠቀም እንችላለን። ለጊዜው ፤ የተመልካች ቁጥሩ 10000 እስኪደርስ አስተያየት ለመሰብሰብ እንዲረዳን ሁሉንም ገጾችህ ከፍት አድርገናቸዋል (  except for the online learning section )

ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን፤

 

ስብከቶች (Preaching)

  • 7768

    ሉቃስ ወንጌል ም። 18 ቁ። 1 __6

    1ሳይታክቱ ዘወትር  ሊጸልዩ  እንዲገባቸው የሚል ምሳሌ ነገራቸው፤ 2እንዲህ ሲል፤  “በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። 3በዚያችው ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፤ ወደ እርሱም እየመጣች፣ ‘ከባላጋራዬ ፍረድልኝ’ ትለው ነበር።  4 አያሌ ቀንም አልወደደም ፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፤ ‘ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ፣ ሰውንም ባላፍር፣ 5ይህች መበለት ስለምታደክመኝ፣ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ  እፈርድላታለሁ አለ።’  6ጌታም አለ፤ “ዓመፀኛው ዳኛ...

  • 6146

    ቀሲስ ሕብረት የሺጥላ፣ በስብከታቸው ከዚህ በታች ያሉትን እና ሌሎች ጥያቄዎችን ያብራራሉ፤ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (link ) በመጫን ስብከቱን ያድምጡ።

    1. የመላእክት አፈጣጠር
    2. የመላእክት ቁጥር ሰንት ነው?
    3. መላእክት ሰራቸው ምንድን ነው ?
    4. ማማለድ ምን ማለት ነው 

  • 6216

    (ኦሪት ዘፍጥረት ም.22  ቁ. 1.)

    ከነዚህ ነገሮች ቦኃላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው። እንዲህም አለው። አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፣ እንሆ አለሁ አለ። የምትወደውን አንድ ልጅህን ይሥሀቅን ይዘህ ወደሞርያም ምድር ኺድ እኔም በምነግርህ ባንድ ተራራ ላይ በዚያ ምሥዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ። አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፣ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሐቅን ከርሱ ጋር ወሰደ፣ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ ተነስቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ።  (ኦሪት ዘፍጥረት ም.22  ቁ. 1.)

    ከዚህ ኃይለቃል...

  • 6172

    ማቴዎስወንጌል ም. 4 ቁ - 1

    ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስወንጌል ም. 4 ቁ - 1

    ከዚህ ኃይለቃል በመነሳት ቀሲስ ሕብረት...

  • 5217

    "እንሆ የእህትሽ የሰዶም ኀጢአት ይህ ነበረ። ትዕቢት ፣ እንጀራን መጥገብ ፣ መዝለልና ሥራ ምፍታት በርሷና በሴቶች ልጆቿ ነበረ ፣ የችግረኛውንና የድሃውንም እጅ አላጸናችም። " ሕዝቃኤል 16 ቁጥር 42

    ቀሲስሕብረትየሺጥላ፣ ከዚህ ኃይለቃል በመነሳት፣በስብከታቸውከዚህበታችያሉትንእናሌሎችጥያቄዎችን...

    Read more: የሰዶም ኀጢአት

  • 2227

    የያቆብ መልእክት

    በመከራ ላሉ የተሰጠ የተስፋ መልእክት።

    {youtube}https://youtu.be/ss8oae-j8lQ{/youtube}

    {youtube}https://www.youtube.com/watch?v=ss8oae-j8lQ{/youtube}

     

ማስታወቂያዎች

Login Form