(ኦሪት ዘፍጥረት ም.22 ቁ. 1.)
ቀሲስ ሕብረት የሺጥላ፣ በስብከታቸው ከዚህ በታች ያሉትን እና ሌሎች ጥያቄዎችን ያብራራሉ፤ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (link ) በመጫን ስብከቱን ያድምጡ።
ከነዚህ ነገሮች ቦኃላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው። እንዲህም አለው። አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፣ እንሆ አለሁ አለ። የምትወደውን አንድ ልጅህን ይሥሀቅን ይዘህ ወደሞርያም ምድር ኺድ እኔም በምነግርህ ባንድ ተራራ ላይ በዚያ ምሥዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ። አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፣ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሐቅን ከርሱ ጋር ወሰደ፣ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ ተነስቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ። (ኦሪት ዘፍጥረት ም.22 ቁ. 1.)
- " ከነዚህ ነግሮች ቦኃላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው።" ይህ ምን ማለት ነው። ከየትኞቹ ነገሮች ቦኃላ ?
- ጣኦት ከሚያመልኩ ሰዎች ጋር ይኖር ነበር። ስለዚህ ከሀገሩና ከቤተሰቡ መሰደድ ነበረበት
- ከአጎቱ ልጅ ከሎጥ መለየት ሌላው ፈተና ነበር፤
- አግብቶ ሲኖር በረሃብ ተሰዶ ነበር፣ በንጉስ ሚስቱን ተቀምቶ ነበር፤ . .. ..
- በዚህ ምድር ላይ ብዙዎቻችን ለራሳችን ተስፋ እንሰጠዋለን። ያላገባ ባገባ አርፋለሁ ይላል፣ ሥራየሌለው፣ሥራ ባገኝ ይላል፣ ተማሪው ትምህርቴን ሰጨርስ ይልስል፣ ... ግን እንዲህ ይታረፋል ወይ ነው ጥያቄው። አብርሃም ብዙ ታላላቅ ፈተናዎችን ካለፈ እና አርፋለሁ ባለበት ሰአት ከነዛ የበለጠ ፈተናን ተፈትኗል፣ ለምን?
- እግዚአብሔር አብርሃመን "አብርሃም ሆይ" አለው አብርሃምም፣ "እንሆ አለሁ አለ" ። አብርሃም የእግዚአብሔርን ድምጽ ያውቃል።
- እግዚአብሔር ተነስቶ አብርሃምን አልፈተነውም። እዮብን ለመፈተን ሰይጣን ከመላእክት ጋር እንደተሰበሰበ ፣ እንዲሁ ሰይጣን አብርሃምን ፈተነው።
Comments powered by CComment