=> ቀን:-   05-11-2013 ዓ.ም
=> ቦታ:-   ነቅዐ ሕይወት(ወለህ ጉባኤ ቤት)
=> መርሀግብር:- የመንፋሳዊ ተቋማት ነባራዊ ህይወትና ልምድ ልውውጥ።

ጠያቂ:- መ/ር ያሬድ
ተጠያቂ(ልምድ አካፋይ):- ዲ/ን ኢሳይያስ  

፩:- የዘመናዊው ሥነ-መለኮት አስተምህሮና የሥርዓት እንዲሁም የትሕርምት ሕይወት ምን ይመስላል?

፪:- የቴዎሎጂያን እና ኮሌጅ የንባብ ባህል ምን ይመስላል?

፫:- ለጉባኤ ቤት ያለን አመለካከት፣ ለሕዝብ ማድረግ ስላለብንና ለዋግ አገረ ስብከት ምን መሥራት አለብን ብለህ ታስባለህ(እናስባለን)?

        *** መልስ ***
፩:- በዘመናዊ አስተምህሮ ያለን እይታ የተሻለ እንዲሆን አለማቀፋዊ የሆኑ ታሪኮችና የተለያዩ ቤተ እምነቶች ስነ-መለኮታዊ እይታ በመማርና ማስተማር በቅድመ ትምህርት መጀመሪያ አመት ከሚማሩት አስተምህሮዎች ዋነኞቹ እንደሆኑ በማብራራት የአስተምህሮውን ስፋትም ከዝርዝር ይዘቶቹ ጋር በአጭሩ ለመግለጽ ሞክረዋል።

፪:- የንባብ ባህልን በሚመለከት ዲ/ን ከተናገራቸው መካከል በጥሩ መንገድ ሊታይ የሚገባው ነገር የንባብ ባሕልን የሚያዳብሩበት በመጽሐፍ የታጨቀ ቤተ-መጽሐፍት መኖር ጎልቶ የተመዘገበ ሲሆን እንደ ፈተና ኦርቶዶክሳዊና ኢ-ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮዎች የሚያስተናግዱ መጽሐፍት መኖር ከአለማቀፋዊ እውነት እና ትምህርት አንፃር ለጥናት ተብሎ ቢታሰብም ለአንጻራዊ ስነ-መለኮታዊ ትምህርት አና ጥናት ሲባል መሠረት የሌላቸውን የቲዮሎጂ ተማሪዮች ከማነጽ ይልቅ የሚያጠፉበት አጋጣሚዎች እንዳሉም በማሰብ ጥንቃቄ ላይ ትልቅ ትኩረት መስጠት እንዳለብን በውይይቱ ምክረሀሳብ ተጠናቋል።

፫:- ቲዮሎጂያን ለጉባኤ ቤት ፣ጉባኤ ቤቱ ለቲዮሎጂያን ያለውን አመለካከት በሰፊው ታይቶ ምክረሀሳቦችም ቀርበው ውይይቱ ተጠናቋል።
ለሁላችሁም(ለሁላችንም) እንኳን አደረሳችሁ/ሰን።
መልካም!

Comments powered by CComment