ሉቃስ ወንጌል ም። 18 ቁ። 1 __6
ከዚህ ኃይለቃል በመነሳት ቀሲስ ሕብረት የሺጥላ፣ በስብከታቸው ከዚህ በታች ያሉትን እና ሌሎች ጥያቄዎችን ያብራራሉ፤ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (link ) በመጫን ስብከቱን ያድምጡ።
1ሳይታክቱ ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌ ነገራቸው፤ 2እንዲህ ሲል፤ “በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። 3በዚያችው ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፤ ወደ እርሱም እየመጣች፣ ‘ከባላጋራዬ ፍረድልኝ’ ትለው ነበር።
4 አያሌ ቀንም አልወደደም ፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፤ ‘ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ፣ ሰውንም ባላፍር፣ 5ይህች መበለት ስለምታደክመኝ፣ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ።’ 6ጌታም አለ፤ “ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ። 7እግዚአብሔርስ እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? 8እላችኋለሁ፤ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?” ሉቃስ ወንጌል ም። 18 ቁ። 1 __6
- መጸልይ ያለበት ማነው ?
- በስራ ስባክን ውዬ ደክሞኝ ነው የምገባው። እንዲህ ደክሞኝ ባልጸልይስ ?
- እግዚሔር እኔን አያውቀኝም? የምፈልገውንስ አያውቅም? ካወቀ ለምን አይሰጥኝም ለምን እጸልያለሁ? ባልጸልይስ
- ለመጸለይ ግድ መቆም አለብኝ፣ ደክሞኛል፣ አሞኛል . . . ?
- ጸሎት አልችልም። ምን ብዬ ልጸልይስ
- በደዌ ተይዤ በዚህ ህመም ላይ እንዴት ልጸልይ፤
- ሁሉ ሞልቶልኛል፣ ለምን እግዚአብሔርን እጨቃጨቃለሁ፣
- በምጸልይ ጊዜ ሃሳቤ ይበታተንብኛል፣ በተመስጦ መጸለይ አልችልም፣ እንዲህ ከሚሆን ባልጸልይስ?
- ለምን በጸሎት መጽሐፍ እጸልያለሁ፣ መጻህፍቱ የኔን ችግር አያወሩ . . .
- የጸሎት እናት ማን ናት ?
Comments powered by CComment