ከአመታት በፊት፣ አንድ መንፈሳዊ ወንድሜ፣ ( ዳናኤል ሽፈራው) ከወንድሞች ጋር በመሆን በማሰራት ላይ ስላለው የአብነት ትምሀርት ቤት ( በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት
ወለህ ደብረገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ) እንዲያገለግል አንድ ድረገጽ እንድሰራለት ጠየቀኝ (መጋቢት 2001)። በነጻ የሚያስተናግዱ ድርጅቶችህን በመጠቀም (  free hosting companies) የ ፕሮጀችቱን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ድረገጽ ሰራን። በወቅቱ የነበረው የማህበራዊ ድረገጽ ( social media ) ተደራሽነት ውስን በመሆኑ የዚህ ድረገጽ መኖር፣ ፎቶግራፎችን ለማጋራት፣ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ ለማየት፣ ቀጣይ ሰራዎችን ለመጠቆም፣ ረድቷል። 

ይህ በንዲህ እንዳለ፣ በአሜሪካን የምትኖር እህቴ ( ፍጹም አበቅየለ ) ባደረገችልኝ እገዛ  abinetschool.com የሚለውን ስም (domain name) በመግዛት እራሱን የቻለ ድረግጽ እንዲሆን ጥረት አደረንግን ። ሆኖም ፕሮጀክት በባህሪው የጊዜ ገደብ ያለው በመሆኑና የማህበራዊ ድረገጽ ተደራሽነት በመጨመሩ፣ የአብነት ትምህርት ቤት ድረገጻችን ያለ አርኪ አገልግሎት ለበርካታ ጊዜያት ልናስቀምጣት ችለናል።

በገነተ ጽጌ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ትምሀርት ቤት የሚሰጠውን የአራት አመት ኮርስ ካጠናቀቅኩኝ ቦኃላ (ጳጉሜ 2006 ዓ.ም.)፣ ባለችኝ ትነሽ እውቅት ይህንን ድረገጽ ለመጠቀም ጥረት ሳደርግ የቆየሁ ቢሆንም በሥራ ብዛት (በዓለማዊ ሥራ በመጠመዴ) በቂ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ አባቶች፣ ወንድሞችና እህቶችጋር ተገናኝቼ ወደፊት ላራምዳት አልቻልኩም። እስከዚያው ግን ከሰንበት ትምሀርትቤት አስተማሪዎቼ (በተለይመ መምህር እንዳለ ተረፈ ) ለመማሪያ ማጣቀሻነት (reference materials) የተሰጡኝን እና እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የድምጽ ቅጅዎችን ለሁሉም እንዲዳረስ በማሰብ በዚህ ድረገጽ ላይ አጋርቻቸዋለሁኝ። በተጨማሪም  የዚችን ድረገጽ ታሪካዊነቷን ለመጠበቅ፣ የወለህ ደብረገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ፕሮጀችት ፎቶዎችን ተቀምጠዋል። እንደወንድሞች ፈቃድ ለሌሎች ትመህርት ይሆን ዘንድ፣ እየተከታተልን እናጋራለን።

ዋናው የእዚህ ድረገጽ አላማ እንዲሆን የምንመኘው ወንጌል ለሁሉ እንዲዳረስ ፣ በግልም ይሁን ከተለያየ ቦታ እንደኔው ጀማሪ ከሆኑ ክርስቲያኖች የሚቀርቡልንን መንፈሳዊ ጥያቄዎች ከመምህራን ጋር በመሆን በማጣቀሻ የተደገፈ መልስ እንዲያገኙ ማድረግ ነው። ለጊዜው ከድምጹ ባለቤቶችም ሆነ ድምጹን ከቀረጹት ባለሞያዎች የተገኘ ምንም አይነት ፈቃድ የለንም። ለወደፊቱ ላሰብናቸው መጣጥፎችም እንዲሁ።

አላማችን በተፈለገ ጊዜም በቀላሉ ይገኝ ዘንድ በመልክ መልኩ የተለያዩ ስብከቶችን እና መጣትፎችን ማስቀመጥ ነው። በተለይም በገነት ጽጌ ሰንበት ትምህርት ቤት ያለፋችሁ እግዚአብሔር ጸጋውን ያበዛላቹ ወንድሞችና እህቶች የምትጽፏቸውን መጣጥፎች በዚህ ድረገጽ በማጋራት ተደራሽነታቸውን በማሳደግ ለብዙዎች ህይወት እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል።  

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

 

email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ስብከቶች (Preaching)

  • 3372

    ሉቃስ ወንጌል ም። 18 ቁ። 1 __6

    1ሳይታክቱ ዘወትር  ሊጸልዩ  እንዲገባቸው የሚል ምሳሌ ነገራቸው፤ 2እንዲህ ሲል፤  “በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። 3በዚያችው ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፤ ወደ እርሱም እየመጣች፣ ‘ከባላጋራዬ ፍረድልኝ’ ትለው ነበር።  4 አያሌ ቀንም አልወደደም ፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፤ ‘ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ፣ ሰውንም ባላፍር፣ 5ይህች መበለት ስለምታደክመኝ፣ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ  እፈርድላታለሁ አለ።’  6ጌታም አለ፤ “ዓመፀኛው ዳኛ

    ...

    Read more: ዘወትር ጸሎት

  • 2626

    ቀሲስ ሕብረት የሺጥላ፣ በስብከታቸው ከዚህ በታች ያሉትን እና ሌሎች ጥያቄዎችን ያብራራሉ፤ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (link ) በመጫን ስብከቱን ያድምጡ።

    1. የመላእክት አፈጣጠር
    2. የመላእክት ቁጥር ሰንት ነው?
    3. መላእክት ሰራቸው ምንድን ነው ?
    4. ማማለድ ምን ማለት ነው 

    Read more: መላእክት

  • 2659

    (ኦሪት ዘፍጥረት ም.22  ቁ. 1.)

    ከነዚህ ነገሮች ቦኃላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው። እንዲህም አለው። አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፣ እንሆ አለሁ አለ። የምትወደውን አንድ ልጅህን ይሥሀቅን ይዘህ ወደሞርያም ምድር ኺድ እኔም በምነግርህ ባንድ ተራራ ላይ በዚያ ምሥዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ። አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፣ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሐቅን ከርሱ ጋር ወሰደ፣ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ ተነስቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ።  (ኦሪት ዘፍጥረት ም.22  ቁ. 1.)

    ከዚህ ኃይለቃል

    ...

    Read more: አብርሃም

  • 2644

    ማቴዎስወንጌል ም. 4 ቁ - 1

    ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስወንጌል ም. 4 ቁ - 1

    ከዚህ ኃይለቃል በመነሳት ቀሲስ ሕብረት

    ...

    Read more: ክርስቲያናዊ ጾም

  • 2149

    "እንሆ የእህትሽ የሰዶም ኀጢአት ይህ ነበረ። ትዕቢት ፣ እንጀራን መጥገብ ፣ መዝለልና ሥራ ምፍታት በርሷና በሴቶች ልጆቿ ነበረ ፣ የችግረኛውንና የድሃውንም እጅ አላጸናችም። " ሕዝቃኤል 16 ቁጥር 42

    ቀሲስሕብረትየሺጥላ፣ ከዚህ ኃይለቃል በመነሳት፣በስብከታቸውከዚህበታችያሉትንእናሌሎችጥያቄዎችን

    ...

    Read more: የሰዶም ኀጢአት

ማስታወቂያዎች

Login Form