አቤላክ ባኮስ,
ተወዳጆች እንደምን አላችሁ?
አንድ በኅብረት ማየት ያለብን ነገር ማቅረብ ፈልጌ ነው አንዳንድ አሳብ እንድታጋሩ ተዘጋጁ፡፡
ወለህ ነቅዐ ሕይወት ጉባኤ ቤት ከተመሠረተበት ዕለትና ሰዓት ጀምሮ አከባቢያዊ ፈተና ቢጋረጥበትም የተመሠረተበትን ዓላማ ለማሳካት ሐዋርያዊ እንቅስቃሴውን በከተማም ሆነ በገጠር እያፋጠነ ይገኛል፡፡
ለዚህም ብዙ የአገልግሎቱ ደጋፊ ምእመናን ያሉት መሆን እየቻለ ነው፡፡
ነገር ግን አሁን ያለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በከተማም ይሁን በገጠር ለአማኞቹ በሚገባቸው መልኩ ሳይሆን ደስ እንዳለን የፈለግነውን ሁሉ እየጫኑ መመለስ እየሆነ ስለሆነ ምእመናንን ባሳተፈ በአዲስ መልክ ለምእመናን በሚመጥን መልኩ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቶ ለሰው ሕይወትም እውቀትም መሆን በሚያስችል መንገድ ቀርጾ የአማናዊት ሃይማኖታችን መመርያዎች የሆኑ ሦስቱን ምስጢራት ለይቶ እያስተማረ ይገኛል፡፡እኒህም፡-
1.ዶግማ
2.ሥርዓት
3.ትውፊት ናቸው
1.ዶግማ ማለት በዘመንና በጊዜ መቀየር ይቀየራል ተብሎ የማይታሰብ በሰው አእምሮ መጠን ይመጠን ተብሎም መቅለል የማይችል የማይቀየር እና የማይሻሻል የማይለወጥ ፅኑዕ መሠረተ እምነት ማለት ነው፡፡
ይህም:-
-ስለነገረ እግዚአብሔር ያለውን ትምህርት አንድነቱንና ሦስትነቱን
-ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ከሦስትነቱ ከአንድነቱ ሰይወጣ ከድንግል ማርያም ሰው መሆኑን
-ስለ ድንግል ማርያም ድንግልና እና ወላዲተ አምላክነት እንዲሁም አማላጅነት
-አንዲት ስለሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ቅድስት መሆን ኩላዊነትና ሐዋርያዊነት
-ስለመላእክት ተራዳኢነት እና ተልእኮ
-ስለ ቅዱሳን ተጋድሎና ቅድስና እንዲሁም አማላጅነት እና ቃል ኪዳን
-ስለመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛነት እና ቅዱስነት ሌላውንም ያካተተ ነው፡፡
2.ሥርዓት
ሥርዓት ማለት መለኪያ ደንብ አጥር ማለት ነው ቤተ ክርስቲያን ያለ ሥርዓት መኖር አትችልም
ሁሉን በሥርዓት አድርጉ እንዳለ ሐዋርያው
ይህም
-ስለ ማኀሌቱ ኪዳኑ ቅዳሴው
-ስለመግባት መውጣት
-በውስጥ ስለሚፈጸመው አገልግሎት ሁሉ
-እንዲሁም ምእመናን በቤታቸው በሥራ ቦታቸው የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴያቸው ሁሉ ሊኖሩት ስለሚገባው ሥርዓት እና ደንብ
-ስለ የልጆች አስተዳደግ አበላል አለባበስ በሙሉ አኗኗር ማሳየት፡፡
3.ትውፊት
ትውፊት ማለት ቅብብል ርክክብ ውርርስ ማለት ነው፡፡
ይህም
-ቁሳዊ
-ቃላዊ
-ሕይወታዊ ትውፊት አለ
-ቁሳዊ የምንለው መጻሕፍትን አድባራትን በሙሉ ንዋያትን ያካተተው ነው
-ቃላዊ የምንለው በቃል ሲተላለፍ የመጣው ያልተጻፈው ሁሉ ነው
-ሕይወታዊ የምንለው ኦርቶዶክሳዊ የሆነው እውነተኛ አኗኗር ነው፡፡
ወለህ ነቅዐ ሕይወት ጉባኤ ቤት በየዓመቱ በክረምት እየሰጠ ያለው ስልጣናም የዚህ አካል ነው ኦርቶክስን በትዳሩ በሥራው በኑሮዉ ሁሉ የሚገልፅ ሰው መፍጠር
መሪ ቃላችንም ንግበር ሰብአ (ሰው እንፍጠር) የሚል ነው፡፡
በዚህ ውይይት አሳብ በመስጠት ኦርቶዶክሳዊነትን በተግባር እናሳይ እላለሁ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Comments powered by CComment