በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ።

የምርቃት ጥሪ ለሁላችሁም።

ለቤተክርስቲያናችንም ሆነ ለሀገራችን ተስፋ የሚሆን ትውልድ ለማፍራት የተገነባው እና በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የወለህ ነቅዐ ሕይወት የመጽሕፍት ትርጓሜ ትምህርት ቤት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የካቲት 10 ቀን 20016 ዓም ይመረቃል። በዚህም እለት ለአለፉት አምስት ዓመታት ሲማሩ የነበሩ ደቀመዛሙርትም ይመረቃሉ። ስለሆነም እነደእግዚአብሔር ቸርነት በእለቱ በመገኘት የጉባኤ ቤቱን ፍሬ በማየት ፈጣሪአችንን አብረን እንድናመሰግን ከታላቅ አክክብሮት ጋር ጠርተንዎታል።

ረዳኤተ እግዚአብሄር አይለየን!

የወለህ ደብረ-ገነት ቅድሰት ማርያም ቤተክርስቲያን ልማት ሕዋስ።

 

Comments powered by CComment