አቤላክ ባኮስ, 
ከይሲ ዘፈጠርከ ይሳለቅ ላዕሌሆሙ 
መዝ 103:(4:)26
የፈጠርከው ዘንዶ ይዘብትባቸዋል
በዚህ ክፍል ክፉ የሆነው ጠላታችን እባብ ዘንዶ ተብሎ ሲጠራ እንሰማለን
በዚህ የተጠራበትም ምክንያት አለው:-
-እባብ ተንኮለኛ ነው በተንኮሉ
-እባብ መርዙ ጎጅና ገዳይ ነው በጎጅነቱ
 -ይህም በብዙ መንገድ ሊተረጎም የሚችል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው ነገር ግን ከዚህ በመቀጠል ስለሁለት እንመለከታለን!


1.ስለ ቀደመው ሐሳዊ አምላክ
የቀደመው ሐሳዊ ዲያብሎስ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘንዶ ተብሎ ተገልጿል ዘፍ ኢሳ 14 ራዕ 13
2.ከሱ የሚመጣው ሐሳዌ መሲህ ነው
ይህ ሐሳዌ መሲህ በሰይጣን ታግዞ
የሚመጣ ብዙ ሐሰተኞችን የሚያስነሣ አሰልፎ የሚመጣ ክፉ የክፉ ልጅ ነው ይህንም መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ
ዘንዶ እያለ ይጠረዋል 
እግዚአብሔር አብ ለባሕርይ ልጁ ለወልድ መምጣት የእውነት ነቢያትን አስነስቶ የእውነት ትንቢትን እንደ አናገረ ሰይጣንም ለግብር ልጁ ለሐሳዌ መሲህ ሰይጣን በእባብ ገላ ተሰውሮ በማሳቱ እባብ ዘንዶ እንደተባለ እሱ ያደረበት አሳቹ ሰውም እባብ ተባለ!
ይህ የሰይጣን ማደሪያ የሆነው እባብ በዓለም ሲገለጥ የሰውን ሁሉ ልብ ይሰልባል ብዞችንም ያስከትላል እሱ የተከተሉት ሁሉም የእሱን ግብር ከመፈጸም አያርፉም ግብሩም ርኩሰትን በደልን ደም ማፍሰስን በቃኝ አለማለት ነው፡፡
የጭካኔ ጥግ አልባነት ይሰፍናል ሰው እንደቅጠል ይረግፋል ይህም አያረካም ምን ቀረኝ ብለው እሰከ መፈለግ መድረስ ነው ይህን ሁሉ አድርገው ምንም እንደ አደረጉ አይሰማቸውም ያደረባቸው ጸላኢ እንደመልካም እንዲቆጥሩ እንጂ እንዳጠፉ እንዲያስቡ አያደርግምና የጥፋት ዘመን ይሉሀል ይህ ነው፡፡
አእምሮ አንዳለ አይቆጠርም 
ሁሉም ያለበቃኝ ይፈጸማል ይህ
ነው ዓለምን በጦርነት አደጋ ውስጥ የጣላት፡፡ 
 ስለዚህ ነው ሀገራችንም የዚህ የክፉ እባብ ሴራ ጥላውን ጥሎባት
 ከጸሎት ቤቶች ይልቅ ጭፈራ ቤቶች
 ከንጽሕና ይልቅ ርኩሰት 
ከምጽዋት ይሕቅ ስርቆት
ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ 
ከአንድነት ይልቅ መከፋፈል 
ከእምነት ይልቅ ዘረኝነት በልጦ እረርስ በርስ ይህ ነው ተብሎ በማይነገር  የዕበደት ግበብር ለብዙ ዓመታት ደም እንደገበረች ያለችው፡፡
የግፍ ሞት የማይደርሰበት አከባቢ የለም በሁሉም አከባቢዎት መምንም የሰላም ጠብታ የሌለ ቢሆንም በሰሜኑ ክፍለ ኢትዮጵያ እና በወለጋ እየተፈጸመ ያለው እልቂት ግን ይህ ነው ተብሎ የማይነገር እና የማይታሰብ ነው፡፡
የእባቡ መርዝ ከአካል ተሰራጭቶ እንዲጎዳ እኛንም  እየጎዳን ያለን ይህ ነው፡፡
ሰው ደኅና ነኝ ይላል ከዚህ ክፉ መንፈስ ከሆነው የእባብ መርዝ ግን የሚድን አይመስለኝም!!
መፍትሔው 
ያለመሰልቸት ስመ እግዚአብሔር መጥራት
በእምነት መጽናት 
በንስሐ ሕይወት መኖር
ሥጋ ወደሙ መቀበል 
በፍቅር መመላለስ
ጥላቻን አጥብቆ መጸየፍ
ለዘረኝነት ቦታ አለመስጠት 
ግፍ ለሚደርሰባቸው ወገኖች ማዘን ለተቸገሩት መራራት
ለእውነት መቆም ነው፡፡
ይህንም እንቢ ብሎ ነው እንጂ እንድንፈጽም የሚፈቅድ ዓለም አይኖርም ውጊያውም ከዚህ ላይ ነው፡፡ 
እናስብ እናስብ እናስብ!!!

አቤላክ ባኮስ, [12/09/2022 6:13 am]
"ወይትአቀቡ ክልኤሆሙ፡፡
ሁለቱም ይጠባበቃሉ " ማቴ 9;
ተወዳጆች እንደምን አላችሁ?
እንኳን አደረሳችሁ?
አዲሱ ዘመን የእውነት አዲስ ይሁንልን 
በነገረ ሃይማኖት አዲሱ ጉዳይ የአምላክ ሰው መሆን ነው፡፡
 አምላክ ሰው ሆነ ብሎ ማስተማር ለብዞች የሚጨንቃቸውም ነገሩ አዲስ ስለሆነ ነው፡፡
ነገር ግን ራሱ ሊሆን የወደደውን እኛ ስለሆነው ማስተማር አያሳፍርምና በዚህ ደስተኞች ነን፡፡
 ስለ ሰው ሲል አምላክ ሰው ሆነ ከሰው 
ጋርም ኖረ ሰውንም አስተማረ እንደመምህርነቱም በቅርበት እየተጠየቀ እየመለሰ አስረዳ የመመለስ ጥበቡም ጎልቶ የሚታወቀው አብዝቶ በምሳሌ መመለሱ ነው፡፡
በምሳሌ ከተመለሱ መልሶች አንዱም ይህ በማቴዎስ 9 ላይ ለተጠየቀው ጥያቄ የመለሰው መልስ ነው፡፡
 ቃሉን ሐዋርያው እንዲህ ዘግቦልናል
"በዘያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደርሱ ቀርበው እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ለምንድን ነው? አሉት
 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊያዝኑ ይችላሉን?
 ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል በዚያ ጊዜም ይጦማሉ፡፡
 በአረጀ ልብስ አዲሱን  እራፊ የሚያኖር የለም መጣፊያውም ልብሱን ይቦጭቀዋል መቀደዱም የባሰ ይሆናል
በአረጀ አቁማዳ አዲሱን የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም ቢደረግ ግን አቁማዳውም ይፈነዳልና ጠጁም ይፈሳል፡፡
ነገር ግን አዲሱን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል ሁለቱም ይጠባበቃሉ፡፡ 
ይህ ከቁጥር 14 እስከ 17 ያለው ምንባብ ነው
ለጊዜው የትምህርቱ ይዘት ሐዋርያት ከጌታ ጋር ሳሉ እንደልባቸው ሲሆኑ ያዩ አርድዕተ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርትህ ለምን አይጾሙም? ላሉት ጥያቄ ራሱን በሙሽራ ሐዋርያትን በሚዜዎች መስሎ እኔ በሞት ስወሰድ ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ በዕርገት ስወሰድ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው የሥራ መጀመሪያቸው ይሆን ዘንድ ከጰራቅሊጦስ ጀምረው ይጦማሉ 
አሁን ጀምሬ ጡሙ ብላቸው ግን ገና ባልበረታ ሰውነት ያሉ ናቸውና እነሱም ይጎዳሉ ጦሙም ፍጹም አይሆንም ሲበቁ ግን ሁለቱም ይጠባበቃሉ እነርሱም ጦሙን አክብረው ይጦሙታል ጦሙም ዋጋ የሚያሰጥ ፍጹም ጦም ይሆናል  የሚል መልስ ነበር፡፡   
አሁን እኛ ግን ከዚህ  የምንፈልገው ጉዳይ ቢኖር በአዲሱ ዘመን ሊኖረን ስለሚገባው  ስለራሳችን  አዲስ ሕይወት ነው፡፡
ታዲያ ይህ ከአዲስ ዓመት ጋር አገናኘው?
ያልን እንደሆነ እንዴት አይገናኝም?
"ሁለቱም ይጠባበቃሉ" 
አዲሱን ዘመን አዲስ ልብ አዲስ መንፈስ አዲስ ሰውነት ይዘው  የጀመሩት እንደሆነ ዘመኑ ሰውነትን ሲጠብቅ ሰውነትም ዘመኑን ሲጠብቅ ሁለቱም እርስ በእርሳቸው ይጠባበቃሉ ያለበለዚያ  ዘመኑ አዲስ ሰውነት ያረጀ ከሆነ ለዘመኑ የሚስማማ ሰውነት ባለመኖሩ አዲሱ ዘመን በአሮጌው ሰውነት ይባላሻል አሮጌው አዲሱን ይዞ ይጠፋል ለዚህ ነው ብዙ ዘመን ዘመኑ ታደሰ  እንኳን ለአዲሱ ዓመት  አደረሳችሁ? ታደሰልን  ስንል ኑረን አዲስ ሰውነት ባለመኖሩ እረርስ በርስ ከመጠፋፋት ከመቦጫጨቅ ከመነካከስ ያልዳነው እንደ ሕዝብ ስናይ ሀገራችን ሰው አልባ ጭቀቆናና አምባ ገነንነት የነገሠባት የእውራን መሪዎች የበዙባት ለሀገሩ ጠላት የሆነ ትውልድ እንደ አሸን እየፈላ ያለባት አሁን አሁን ደግሞ ዓመታትዋን የምትለውጥበትን የባሕረ ኀሳብ ቀመር የሚነቅፉ አክራሪ ጽንፈኞች ብቅ የሚኮንኑባት ለባርነት እንድትገዛ የሚናፍቁ ዜጎች እየተፈጠሩ ያሉባት እየሆነች እያየናት እንገኛለን፡፡
እንደቤተ ክርስቲያንም ስንመለከት ለክብሯ የሚመጥኑ መሪዎች ለሕዝቡ አርዐያ መሆን የሚችሉ መምህራን የሰማይ ሣር የምድር  ኮከብ የሆኑባት ሥርዓቷን የሚያስከብር ለትውፊቷ የሚቆረቆር ሰው እየጠፋ ያለባት ከጥቂቶቹ በስተቀር ራሱን አሳልፎ እስከ መስጠት የሚደርስ አገልጋይ የታጣባት የቀናው የአባቶቻችን መንገድ ሁሉ እየተዘጋ ያለበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን ታዲያ ለዚህ አዲስ ዘመን ይህን ሁሉ የተረዳ እና እደግልም እንደ ማኅበረ ሰብም የተረዳውን የአቅሙን ያክል ለመቅረፍ የሚሮጥ አዲስ ልብ አዲስ መንፈስ ያለው አዲስ ሰውነት ያስፈልጋል፡፡
ይህ የሆነ እንደሆነ አዲሱን ዘመን በአዲስ ሰውነት ማኖር ይሆንና ሁለቱም ይጠባበቃሉ፡፡
ሐዋርያውም
 "በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ፡፡" ሮሜ 12:- ያለው ይህን ነው፡፡
በአሮጌ ሰውነት የተቀበልነው አዲስ ዘመን ምኑን አዲስ ሊሆን ይችላል?
እስኪ አስቡ ብዙ ጊዜ በአል ሲመጣ የምንጨነቀው ስለምኑ  ነው? የምንዘጋጀውስ ስለምኑ ነው?
ይህ ግልፅ ነው፡፡
ሁሌም የምንጨነቀው  
ስለምንበላው 
ስለምንጠጣው 
ስለምንለብሰው 
ስለምንቀመጥበት ነው፡፡
የምንዘገጀውም ስለበአሉ ማማር እና ውበት ነው፡፡
 ይህ ሲባል ግን ሰው በአል ሲደርሰ የቻለውን ያክል አዘጋጅቶ አይቅመስ ማለት አይደለም 
የማይቻለውን ሁሉ ካላገኘሁ ይህ ካልተገዛልኝ  እያሉ ሚስት በባልዋ ላይ ባል በሚስት ላይ የሚያነሡትን መነቋቆር ግነ እንቃወማለን አብዛኞቹ ባለትዳሮች ኑረው ኑረው በአል ሲደርስ ከመደሰት ይልቅ ሲያዝኑ ሲታወኩ ይታያሉ ይህ የሚሆነው አቅምን ያላገናዘበ የበአል መዋያ  ከማሰብ ነው፡፡
በአል ሲደርስ ራስን ለበረከት ለንስሐ ለሥጋ ወደሙ ማዘጋጀት እንጂ በሥጋዊ ጉዳይ በልጅም በምግብም ምክንያት መነካከስ ክርስቲያናዊ ጠባይ አይደለም
በአል ከመምጣቱ በፊት አዲሱን በምን አዲስነት ልቀበል? ብሎ ማሰብ እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡
ይህ ሲሆን ሁለቱም ይጠባበቃሉ ማቴ 9;17
✍እንግዲህ ከበአል ዝግጅት ወጣ ብለን ወደራስ ዝግጅት መመለስ ግድ ይለናል፡፡
ለማለት ይህ ተጻፈ✍
ወለህ ነቅዐ ሕይወት
2015 ዓ.ም
እሑድ የበአል ቀን
ፍኖተ ሰላም በ9.00 ተጻፈ

Comments powered by CComment