yared Mhrete
"፫ቱ ዓለማት"
እንደ አልጄሪያዊው የለውጥ ተመራማሪ ከሆነ ለሰዎች ሦስት ዓለማት አሏቸው ይላል
 እኒህም:--
፩.የአስተሳሰብ ዓለም 
፪.የግኑኝነት ዓለም
፫.የምርት ዓለም ናቸው 
            ፩.የአስተሳሰብ ዓለም
አስተሳሰብ ማለት ሰዎች ከልብ ጠልቀው ወደመንፈሳዊ እሳቤ ሲገቡ የሚታያቸው ግለሰባዊና ማኅበረ ሰባዊ የለውጥ መንሥኤ የሆነው የውስጥ ጉዞ ነው፡፡
ሰው ከሥጋዊ አካል በሻገር  የመንፈሳዊ አካል ባለቤት እንደመሆኑ መጠን በመንፈስ የሚኖር ነው ከዚህም የተነሣ የማሰብ መንገዱ የማይቋረጥበት ሁሉን ከማሰብ የማመንጨት አቅም ያለው የአስተሳሰብ ተገዥ ነው ከአስተሳሰብ ነፃ የሆነ ሰው ከሰውነት እየወጣ ማለት ይቻላል፡፡


ሰው ሆኖ ለመቀጠል አሳቢ መሆን የግድ ነው ብዙ ሰው ለአሳብ ቦታ መስጠት አይወድም ማሰብን እንደ መጨነቅ ይቆጥራል ይህ ግን ረራሱ አለማሰብ ነው አሳቢነትን ከተጨናቂነት አሳብን  ከጭንቀት ጋር ማያያዝ ያለማወቅ ውጤትም ነው፡፡
ሰው በአስተሳሰብ ዓለም ውስጥ ራሱን ካላገኘ ከማሰብ ውጭ ያገኘዋል ይህም ከሚኖረው ዓለም ውጭ እንደመኖር ነው 
አሳቢ አእምሮ ከዓለም ይሰፋል ዓለም ምንም ሰፊ ብትመስልም ከአሳቢዎች አእምሮ ውጭ ግን አይደለችም በዓለም ውስጥ ያለ ዓለምን ያቀፈ በጊዜ ማዕቀፍ ጊዜን ያቀፈ በዘመን ሥር ያለ ዘመንን የመረመረ ማን ነው?
በአካል ውሱን በአእምሮ በዓለም ዳርቻ ዘዋሪና ተስፋፊ የሆነው የሰው ልጅ ነው፡፡
ዓለም የማትወስነው የብስል ሰው አስተሳሰብ ራሱ ዓለም ነው ይህም የአስተሳሰብ ዓለመም ይበባላል ከዚህ አእንዳትወጣ ጠንክረህ አስብ ማሰበብን ከምን ልጀምር? ካልክ ማሰብ የምትጀምረው 
ከማሰብ ነው እልሐለሁ ያለመልካም አስተሳሰብ መልካም ለውጥ አይታሰብም ለሀገርም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን ለግልም ሆነ ለኅብረት ሕይወት የመልካም ለውጥ መነሻው መልካም አስተሳሰብ ነው፡፡
             ፪.የግኑኝነት ዓለም
ግኑኝነት ማለት ሰዎች ያሰቡትን መልካም እሳቤ ወደአንድ አምጥተው ልብ ለልብ የሚገናኙበት የውስጥ ተራክቦ እና ጠልቆ የማሰብ ውጤት ነው የመልካም አስተሳሰብ ተግባሩ ግኑኝነት ነው
 ሰው ምንም አሳቢ ነኝ ቢልም ከሌላው ሰው ጋር  መገናኘት የሚከብደው ከሆነ ገና ማሰብ አልጀመረም ማለት ነው ማሰብ እንደሚገባው እስካላሰበ ድረስ አሁንም አላሰበም እስኪ እናስብ ሰው ከሸው ከሰው መገናኘት እንዴት ሊከብደው ይችላል?
እውን ሰው ከሰው ጋር ጠበኛ ነውን?
አይመስለኝም የጎደለን ነገር ምንድን ነው?
ሌላ ምንም አይደለም በትክክል ከማሰብ የመራቅ ምሥጢረር ነው፡፡
ትክክለኛ ግኑኝነት እንደዲኖረን ትክክለኛ አስተሳሰብ ያስፈልገናል፡፡
የትክክለኛ አስተሳሰብ ውጤቱ ትክክለኛ ግኑኝነት ነውና፡፡
             ፫.የምርት ዓለም
ምርት ማለት ከመልካም ግኑኝነት የሚመጣ የሥራ ስብስብ ነው ሰው ያስባል ይገናኛል ያመርታል ለግለሰብም ሆነ ለማኅበረ ሰብ የመጨረሻ መዳረሻው የምርት ዓለም መሆን አለበት
አስቦ ካልተገናኘ አላሰበም ተገናኝቶ ካላመረተም አልተገናኘም ማለት ነው፡፡
ሥራችሁን ሁሉ በምርታችሁ መዝኑት ምርት የሌለው ሥራ ውጤቱ ድካም ብቻ ነው የትም እንሂድ የትም እንኑር መሆን የሚገባን ግን የምርት ሰው ነው፡፡
ማምረት ያልቻለ አሳቢ ነኝ የሚል ሁሉ አሳቡ ለምን  ጠቀመው? ለምንም
ስለዚህ ሰው ሁሉ ባለበት አከባቢ ደስ ብሎት ማሰብና መገናኘት ማምረት አለበት እንጂ ይህ አይመቸኝም ይህ ይሻለኛል እያለ መክንያት መደርደር የለበትም፡፡ 
በአስተሳሰቡ ተለውጦ አሁን ሥራ መጀመር አለበት እንዴት ልለወጥ? የሚል ካለ?
ለአስተሳሰብ ለውጥ 
መሠረቱ  ትምህርት
ማገሩ ንባብ 
ውበቱ ተግባር ነው
አሁንም የዕውቀት ምርት የመንፈሳዊ ተግባር ምርት እጅጉን ያስፈልገናልና እንበርታ፡፡
 የአስተሳሰብ ዓለም! የግኑኝነት ዓለም! የምርት ዓለም! 
 እናስብ! እንገናኝ! እናምርት እላለሁ
🌳🌳መልካም አዲስ ሕይወት🌳🌳
 ወለህ
ተጻፈ
 የ2014 ዓ.ም ፍጻሜ የ2015 ዓ.ም ጅማሬ ከምሽቱ 2.30
ፍኖተ ሰላም

Comments powered by CComment