ከአመታት በፊት፣ አንድ መንፈሳዊ ወንድሜ፣ ( ዳናኤል ሽፈራው) ከወንድሞች ጋር በመሆን በማሰራት ላይ ስላለው የአብነት ትምሀርት ቤት ( በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት
ወለህ ደብረገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ) እንዲያገለግል አንድ ድረገጽ እንድሰራለት ጠየቀኝ (መጋቢት 2001)። በነጻ የሚያስተናግዱ ድርጅቶችህን በመጠቀም ( free hosting companies) የ ፕሮጀችቱን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ድረገጽ ሰራን። በወቅቱ የነበረው የማህበራዊ ድረገጽ ( social media ) ተደራሽነት ውስን በመሆኑ የዚህ ድረገጽ መኖር፣ ፎቶግራፎችን ለማጋራት፣ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ ለማየት፣ ቀጣይ ሰራዎችን ለመጠቆም፣ ረድቷል።
ይህ በንዲህ እንዳለ፣ በአሜሪካን የምትኖር እህቴ ( ፍጹም አበቅየለ ) ባደረገችልኝ እገዛ abinetschool.com የሚለውን ስም (domain name) በመግዛት እራሱን የቻለ ድረግጽ እንዲሆን ጥረት አደረንግን ። ሆኖም ፕሮጀክት በባህሪው የጊዜ ገደብ ያለው በመሆኑና የማህበራዊ ድረገጽ ተደራሽነት በመጨመሩ፣ የአብነት ትምህርት ቤት ድረገጻችን ያለ አርኪ አገልግሎት ለበርካታ ጊዜያት ልናስቀምጣት ችለናል።
በገነተ ጽጌ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ትምሀርት ቤት የሚሰጠውን የአራት አመት ኮርስ ካጠናቀቅኩኝ ቦኃላ (ጳጉሜ 2006 ዓ.ም.)፣ ባለችኝ ትነሽ እውቅት ይህንን ድረገጽ ለመጠቀም ጥረት ሳደርግ የቆየሁ ቢሆንም በሥራ ብዛት (በዓለማዊ ሥራ በመጠመዴ) በቂ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ አባቶች፣ ወንድሞችና እህቶችጋር ተገናኝቼ ወደፊት ላራምዳት አልቻልኩም። እስከዚያው ግን ከሰንበት ትምሀርትቤት አስተማሪዎቼ (በተለይመ መምህር እንዳለ ተረፈ ) ለመማሪያ ማጣቀሻነት (reference materials) የተሰጡኝን እና እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የድምጽ ቅጅዎችን ለሁሉም እንዲዳረስ በማሰብ በዚህ ድረገጽ ላይ አጋርቻቸዋለሁኝ። በተጨማሪም የዚችን ድረገጽ ታሪካዊነቷን ለመጠበቅ፣ የወለህ ደብረገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ፕሮጀችት ፎቶዎችን ተቀምጠዋል። እንደወንድሞች ፈቃድ ለሌሎች ትመህርት ይሆን ዘንድ፣ እየተከታተልን እናጋራለን።
ዋናው የእዚህ ድረገጽ አላማ እንዲሆን የምንመኘው ወንጌል ለሁሉ እንዲዳረስ ፣ በግልም ይሁን ከተለያየ ቦታ እንደኔው ጀማሪ ከሆኑ ክርስቲያኖች የሚቀርቡልንን መንፈሳዊ ጥያቄዎች ከመምህራን ጋር በመሆን በማጣቀሻ የተደገፈ መልስ እንዲያገኙ ማድረግ ነው። ለጊዜው ከድምጹ ባለቤቶችም ሆነ ድምጹን ከቀረጹት ባለሞያዎች የተገኘ ምንም አይነት ፈቃድ የለንም። ለወደፊቱ ላሰብናቸው መጣጥፎችም እንዲሁ።
አላማችን በተፈለገ ጊዜም በቀላሉ ይገኝ ዘንድ በመልክ መልኩ የተለያዩ ስብከቶችን እና መጣትፎችን ማስቀመጥ ነው። በተለይም በገነት ጽጌ ሰንበት ትምህርት ቤት ያለፋችሁ እግዚአብሔር ጸጋውን ያበዛላቹ ወንድሞችና እህቶች የምትጽፏቸውን መጣጥፎች በዚህ ድረገጽ በማጋራት ተደራሽነታቸውን በማሳደግ ለብዙዎች ህይወት እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
email: