2 የፕሮጀክቱ ዓላማዎችና ግቦች
የወለህ ደብረ-ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አብነት ትምህርት ቤት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ግቦችና ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው::
2.1 ዓላማ

    • የአብነት ተማሪዎችን እንግልት በመቀነስ በአጭር ጊዜ ለአገልግሎት አንዲበቁ ማድረግ
    • ወደዘመናቸን የተሻገረውን የሃገር ቅርስ ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ
    • ሥልጣነ ክህነት ሊቀበሉ የተዘጋጁ ሰዎች በቂ እውቀት የጨበጡ መሆኑን ማረጋገጫ መስጠትና በቂ ትምህርት ላልተማሩት ደግሞ ኣጫጭር ሥልጠና መስጠት
    • ተማሪዎች ከመንፈሳዊ ትምህርቱ ባሻገር ራስን የመቻል አቅም ሊፈጥርላቸው የሚችሉ ሙያዎችን ማስተማር

2.2 ግብ

    • ቤተክርስቲያኒቱ ያላትን የማህበራዊና የልማት መሪነት ሚና ሊወጡ የሚችሉ ደቀመዛሙርትን ማፍራት
    • ቤተክርስቲያኒቱ ያለባትን ፈተና ተቋቁማ የሃዋርያነት ተልዕኮዋን እንድትወጣ ማስቻል
  • ትምህርት ቤቱ እንደናሙና ተወስዶ ተመሳሳይ የአብነት ትምህርት ቤቶች በአገሪቱ እንዲስፋፉ መንገድ መጥረግ    

Comments powered by CComment