3. የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ ፕሮጄክት
3.1 የፕሮጄክቱ ቦታ
የወለህ ደብረ-ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በዋግ ኽምራ መስተዳድር ዞን በሰቆጣ ወረዳ የምትገኝ ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ወለህ ከአዲስ አበባ 682 ኪ.ሜ.፤ ከዞኑ ዋና ከተማ ከሰቆጣ ደግሞ 18 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የሚገኝ ሜዳማ ቀበሌ ነው፡፡ ቦታው ወይናደጋማ የአየር ንብረት አለው፡፡
ወለህ ከኮረም ወደሰቆጣ በሚወስደው መንገድ ላይ ገባ ብላ እንደመገኘቱ መጠን በተወሰኑ መልኩ የመሰረተ-ልማት ተጠቃሚ ነው፡፡ክሊኒክ፣አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤ/ት ፣ መብራት ፣ የመጠጥ ውሃና ጥርጊያ መንገድ አካባቢው ተጠቃሚ የሆነባቸው የልማት ውጤቶች ናቸው::
3.2 የትምህርት ይዘት
ት/ቤቱ መሠረታዊውን የአብነት ትምህርት(ንባብ፣ ውዳሴ ማርያም፤ዳዊትእና መልክኦችን ወ.ዘ.ተ.) የአጠናቀቁትን በመጻሕፍት ትርጓሜ ያሰለጥናል:: የመጻሕፍት ትርጓሜ የሚባለው የብሉይ ፣ የሐዲስ ፣ የመጽሐፈ ሊቃውንትና የመጽሐፈ መነኮሳትን ትርጓሜ ነው:: ከአብነቱ ትምህርት ጎን ለጎን ለሃዋሪያዊ ተልእኮ የሚያበቃቸውን ተጨማሪ መሠረታዊ ትምህርቶች ያስተምራል።እነዚህም ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን፤የቤተክርስቲያንታሪክ፤ሥርዓተቤተክርስቲያን፤ሥርዓተ-ኖሎት፤ግእዝ፤አስተዳደር፤ጤና አጠባበቅ እና ሂሳብ መዝገብ አያያዝ ናቸው።
3.3 ግንባታ
በመግቢያው ላይ በታየው ስእላዊ መግለጫ መሰረት ፕሮጄክቱ የሰባት ህንጻዎችን ግንባታ ያጠቃልላል ::እነዚህም፦
- መማርያ ህንጻ 5. አስተዳደር ህንጻ
- መኝታ ህንጻ 6. ጥበቃ ክፍል እና
- መመገቢያ ህንጻ 7. መጸዳጃ ቤት ናቸው::
- እንግዳ መቀበያ
Comments powered by CComment